RNEST-2005                                                  

RNLogo

ራዲዮ ነጋሺ የተቋቋመው ማርች 9 2005 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነው። የራዲዮ ነጋሺ አመሰራረት የራሱ የሆነ ታሪክ አለው። የራዲዮ ጣቢያው ባለቤት የነበረው ነጃሺ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ማህበር በስዊደን ሬዲዮ ጣቢያውን ከመክፈቱ በፊት ለአባላቱ የሚያደርጋቸው ጥሪዎች ሲኖሩት በወቅቱ ስቶክሆልም ከተማ ውስጥ በነበሩ ሁለት (አንደኛው የመንግስት ደጋፊ አንደኛው ደግሞ ተቃዋሚ በሆኑ) "ኢትዮጵያዊ " የራዲዮ ጣቢያዎች ይጠቀም ነበር። ነገር ግን ይህ ሁኔታ የሚያዛልቅ አልሆነም።

የዚህ መድረክ አላማ እስላማዊ ደዓዋ ከመስጠት በተጨማሪ የሙስሊሙን የእለት ከእለት አኗኗር ለማሳየትና በተለይም በሂደት የሥነ ጽሁፍ ጥበብን ማዳበር የሚቻልበትን መንገድ ለመክፈት ስለሆነ በተለይ በዚህ ረገድ ፍላጎት ያላችሁ ሁሉ ይህንን መድረክ እንድትጠቀሙበት እናሳስባችኃለን።  ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ላይ የተጣለበትን ከሃገሩ የማግለል እርምጃ ማሸነፍ የሚቻለው በማማረርና ተቃውሞን በማሰማት ብቻ ሳይሆን በሃገሩ ጉዳይ ላይ በቀጥታ ተሳታፊ በመሆን ነው። የገዛ ሃገራችንን ሌሎች ሲገልጿት እኛን ለምን አገለሉን ብለን ከማማረር ይልቅ ራሳችንን በተለያዩ መንገዶች መግለጽና መተንተን መቻል አለብን።  እኛ የቤት ሥራችንን መስራት ስንጀምር ብቻ ነው ሌሎችም የሥራዎቻቸውን ጎዶሎነት የሚረዱት። ስለዚህ የቤት ሥራችንን ለመስራት የሚያስፈልገውን ጊዜ እንስጥ እያልን ሥራችን የተሳከ ይሆን ዘንድ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላን እንለምናለን።  

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ!